Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የአካባቢን ሰላምና ጸጥታ ለማሰጠበቅ ስልጠና የወሰዱ በጎፈቃደኞች ወደ ስራ ገቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “እኔ የከተማዬ የሠላም ዘብ ነኝ “በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ ከተለያየ ክፍለ ከተማ የአካባቢን ሰላምና ጸጥታ ለማሰጠበቅ ስልጠና የወሰዱ በጎፈቃደኞች ወደ ስራ መግባታቸውን ከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ፡፡
በጎ ፈቃደኞቹ በየካ፣ በለሚ ኩራ፣ በኮልፌ ቀራኒዮ፣ በቂርቆስ እና በልደታ ክፍለ ከተሞች ነው ስልጠናቸውን የወሰዱት፡፡
በወንጀል መከላከል፣ በህዝብ ደህንነት እና ሰላም እንዲሁም በሰላም እሴቶች ዙሪያ ስልጠናቸውን የተከታተሉ በሺዎች የሚቆጠሩ በጎፈቃደኞች ተመርቀው ወደ ስራ ተሰማርተዋል መባሉን ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በቀሪ ክፍለ ከተሞችም የከተማዋን ሰላምና ደሕንነት ለመጠበቅ ስልጠና በመውሰድ ላይ የሚገኙ መኖራቸውም ተጠቁሟል፡፡
በጠቅላላው ከ27 ሺህ በላይ በጎፈቃደኞች ባሉበት ብሎክ እና ወረዳ የአካባቢያቸውን ሰላም ለመጠበቅ በዝግጅት ላይ ይገኛሉም ነው የተባለው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.