Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን የአገሪቱ ክፍል ያለውን ችግር ለመፍታት በፌዴራል መንግሥት በኩል የሰላም ተደራዳሪ ቡድን ተሰየመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ያለውን ችግር ለመፍታት የሚከተለው የሰላም አማራጭ አገራዊ ጥቅምን በሚያስከብር እና በአፍሪካ ኀብረት አመቻችነት እንዲካሄድ መወሰኑን የፍትህ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ አስታውቀዋል።
 
የፍትህ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት÷ እንደ ብልጽግና ችግሩን ለመፍታት ፓርቲው የሚከተላቸው የሰላም አማራጮች ሕገ መንግስታዊነትን ባከበረ፣ አገራዊ ጥቅምን በሚያስከብር መልኩ በአፍሪካ ኀብረት አመቻችነት እንዲካሄድ የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ እና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
 
በዚህም መሠረት በፌዴራል መንግስት በኩል የሰላም ተደራዳሪ ቡድን መሰየሙን ምንጮቻችን አረጋግጠዋል፡፡
 
የሰላም ተደራዳሪ ቡድኑ አባላት ስም ዝርዝርም የሚከተሉት መሆናቸው ታውቋል፡-
1ኛ. አቶ ደመቀ መኮንን……..ሰብሳቢ
 
2ኛ. ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዎስ…..አባል
 
3ኛ. አቶ ተመስገን ጥሩነህ……አባል
 
4ኛ. አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር….አባል
 
5ኛ. አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን…..አባል
 
6ኛ. ሌ/ ጀኔራል ብርሀኑ በቀለ….አባል
 
7ኛ. ዶ/ር ጌታቸው ጀምበር………አባል
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.