Fana: At a Speed of Life!

በቂርቆስ ክ/ከተማ 108 ማህተሞችና ሀሰተኛ ሰነዶችን ለህገ ወጥ ተግባራት ሲጠቀሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሰር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 4 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወርዳ 4 ጎተራ ኮንዶሚኒየም ውስጥ 108 ማህተሞች እና የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን ለተለያዩ ህገ ወጥ ተግባራት ሲጠቀሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሰር መዋሉን ፖሊስ ገለጸ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባወጣው መረጃ እንዳስታወቀው፥ ወንጀሉን በመፈፀም የተጠረጠሩት ሁለት ግለሰቦች ሀምሌ 1 ቀን 2012 ዓ.ም ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

ተጠርጣሪዎቹ 108 የግል እና የመንግስት መስሪያ ቤት ማህተሞች እንዲሁም 15 ሀሰተኛ ሰነዶች እንደተገኘባቸው የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ማስተባበርያ ሀላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ስለሺ ሸንቁጤ ተናግረዋል።

ከተጠቀሱት ማህተሞች ውስጥ የትምህርት ሚኒስቴ የሙያ ማረጋገጫ ማሕተም እና የተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ህገወጥ ሰነዶች መገኘታቸውንም አስታውቅዋል።

በተያያዘ ዜና ግምታዊ ዋጋቸው ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሆኑ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በተሽከርካሪ በመጫን ወደ አዲስ አበባ ያስገቡ ሁለት ተጠርጣሪዎች ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝም ተገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ ህገ-ወጥ የኮንትሮባንድ እቃዎችን ይዘው የተገኙት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው አቦ ሴራ ፒስታ መንገድ ቴሌ ጫፍ አካባቢ ነው።

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወንጀል መርማሪ ምክትል ሳጅን ማናየ ጫኔ እንደጠቀሱት፥ ተጠርጣሪዎቹ በሲኖትራክ ተሽከርካሪ ከጫኑት 43 ኩንታል ስንዴ ስር 4 ሺህ ኪሎ
ግራም ልባሽ ጨርቅ እና 11 ሺህ 280 የፈረንሳይ ሽቶ አስገብተዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በአጠቃላይ የዋጋ ግምታቸው ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆኑ የኮንትሮባንድ እቃዎችን ደብቀው ወደ አዲስ አበባ ይዞው ሲገቡ ከህብረተሰቡ በደረሰ
ጥቆማ በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸውን አስረድተዋል።

በተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝም መግለፃቸውንም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባወጣው መረጃ አስታውቋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.