Fana: At a Speed of Life!

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ፋሲል ከነማ ኢትዮጵያ ቡናን 3 ለ 0 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ29ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ ኢትዮጵያ ቡናን 3 ለ 0 በማሸነፍ ለዋንጫ የሚያደርገውን ፉክክር አጠናክሯል፡፡
ምሳ ሰዓት በተካሄደው ጨዋታ ሙጅብ ቃሲም ለፋሲል ከነማ ሁለት ጎሎችን ሲያስቆጥር ሱራፌል ዳኛቸው ቀሪዋን አንድ ጎል በፍፁም ቅጣት ምት ማስቆጠር ችሏል፡፡
አፄዎቹ ዛሬ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ነጥባቸውን 61 በማድረስ የፕሪሚየርሊጉን መሪነት ቀሪ ጨዋታ ካለው ቅዱስ ጊዮርጊስ ለጊዜው ተረክበዋል፡፡
ረፋድ በተከናወነ ሌላኛ የሊጉ መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና አዲስ አበባ ከተማን በሙሉዓለም መስፍን እና ሀብታሙ ገዛኸኝ ጎሎች 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.