Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከተማ ከመጪው ሰኔ 27 እስከ 29 የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይሰጣል

አዲ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሰኔ 27 እስከ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ ሦስት ቀናት እንደሚሰጥ ተገለጸ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና አፈጻጸም ዙሪያ ሂደቱን ለመከታተል ከተቋቋመው የኮማንድ ፖስት አደረጃጀት ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
በዚሁ ወቅት እንደተገለጸውም÷ ፈተናው ዘንድሮ ከሰኔ 27 እስከ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ ሶስት ቀናት ይሰጣል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ የፈተና አፈጻጸም ሂደቱን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ÷ ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ ከፈተና ህትመት ጀምሮ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል፡፡
በከተማ አስተዳደሩ በሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች የፈተና ሂደቱ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ የትምህርት መዋቅሩ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የጸጥታ ኃይሎች ጋር በጋራ ይሠራል ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ÷ በ2014 ዓ.ም በከተማ አስተዳደሩ በ179 የመፈተኛ ጣቢያዎች 71 ሺህ 832 ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱና ለሁሉም ተማሪዎች አድሚሽን ካርድ መታደሉን ተናግረዋል፡፡
ዘንድሮ በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች 1 ሺህ 800 ፈታኝ፣ 450 ሱፐር ቫይዘሮች፣ 179 የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎችን ጨምሮ በድምሩ 2 ሺህ 429 የፈተና አስፈጻሚዎች መመደባቸውም ገልጸዋል፡፡
ከቢሮ ጀምሮ እስከ ፈተና ጣቢያዎች ድረስ የፈተናውን ሂደት የሚከታተል ኮማንድ ፖስት መዋቀሩንም የትምህርት ቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.