Fana: At a Speed of Life!

የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተለያዩ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2014 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና በተለያዩ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች መሰጠት ጀምሯል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፣ በሀረሪ ክልል፣ በአፋር እና በኦሮሚያ ክልሎች በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት ፈተናውን በመውሰድ ላይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ የፈተና ደህንነት ለመጠበቅ እና የፈተናውን ሂደት ለመከታተልም ቀደም ሲል የተዋቀረው ኮማንድ ፖስት 10 የፀጥታ አካላት ማሰማራቱ ተጠቁሟል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ 179 የመፈተኛ ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን÷ 71 ሺህ 832 የሚሆኑ ተማሪዎች ፈተናውን እየወሰዱ እንደሚገኙ የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

በሀረሪ ክልል የሚሰጠውን የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በአንድ ፈተና ጣቢያ በመገኘት አስጀምረዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት÷በክልሉ እየተሰጠ ያለው ፈተና ሂደት ፍጹም ሰላማዊና ስነ-ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ እየተከናወነ እንደሚገኝ መመለከታቸውን ገልፀዋል።

በሀረሪ ክልል የ8ተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ላይ 4 ሺህ 900 ተማሪዎች በ26 የፈተና ጣቢያዎች ፈተናቸውን እየወሰዱ ሲሆን÷ ፈተናው እስከ ረቡዕ ሰኔ 29 ድረስ እንደሚሰጥ ተመላክቷል፡፡

በዘቢብ ተክላይ እና ተሾመ ኃይሉ

ተጨማሪ መረጃ ከትምህርት ሚኒስቴር

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.