Fana: At a Speed of Life!

የእርዳታ እህል የጫኑ 21 ከባድ የጭነት መኪናዎች በአብኣላ በኩል ወደ ትግራይ መጓዝ ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ምግብ ድርጅት አማካይነት 21 ከባድ የጭነት መኪናዎች የእርዳታ እህል በመጫን በአፋር ክልል በአብኣላ በኩል ወደ ትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ መጓጓዝ መጀመሩን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
 
የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ውስጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዜጎችን ህይወት ለመታደግ ሁሉንም አማራጮች በመጠቀም የሰብዓዊ እርዳታን ለማቅረብ እንቅስቃሴ መጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡
ውሳኔው ከተወሰነበት ቀን ጀምሮ መድኃኒት፣ የህክምና መሳሪያዎች፣ ገንዘብና አልሚ ምግቦችን በመጫን ረጂ ድርጅቶች በቻሉት መጠን በአየር ትራንስፖርት በየዕለቱ መጓጓዝ መጀመራቸውንም የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አመላክቷል፡፡
 
በዛሬው ዕለትም በዓለም ምግብ ድርጅት አማካይነት 21 ከባድ የጭነት መኪናዎች የእርዳታ እህል በመጫን በአፋር ክልል በአብኣላ በኩል የሰብዓዊ እርዳታ በየብስ ትራንስፖርት ወደ ትግራይ ክልል መጓጓዝ መጀመሩን ነው ያስታወቀው፡፡
 
የኢትዮጵያ መንግስት የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቱን በተሟላ ሁኔታ ለማስኬድ ከተባበሪና ባለድርሻ አካላት ጋር ለመስራት ዛሬም ቁርጠኛ መሆኑንም መግለጫው አጽንኦት ሰጥቷል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.