Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል በህገ-ወጥ ንግድ ተሰማርተዋል በተባሉ ከ23 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል በህገ-ወጥ ንግድ ላይ ተሰማርተዋል በተባሉ 23 ሺህ 303 ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሰዱን የደቡብ ክልል የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የደቡብ ክልል ምክር ቤት የከተማ ልማትና መሰረተ-ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የ2014 በጀት ዓመት አፈጻጸም ገምግሟል፡፡

የደቡብ ክልል የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ማሄ ቦዳ ÷ በበጀት ዓመቱ የንግድና ግብይት ህጎች የማስከበር ስራዎችን ከማጠናከር አኳያ 17ሺህ 378 ድርጅቶች ላይ የማሸግ እርምጃ እና 2ሺህ 144 ድርጅቶች ላይ የቃልና የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም 3 ሺህ 781 ድርጅቶች ላይ የማገድ የተወሰደ ሲሆን ÷በድምሩ 23 ሺህ 303 ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ጠቁመዋል፡፡

በክልሉ የንግድ ሥርዓቱን እያስተጓጎለ ያለውን የደላላ ሚና ለማስቀረትም ከደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ እንዲሁም ከህብረት ሥራ ኤጀንሲ ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ መናገራቸውን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ ፡፡

በውይይቱ የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ሴክተር የደላላ ሚናን በማስቀረት እና ህገ-ወጥ የንግድ ሥርዓትን በመከላከል በኩል በርካታ ተግባራት መከናወናቸው ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.