Fana: At a Speed of Life!

በጂቡቲ የሚገኘው ታሪካዊው የኢትዩጵያ ኤምባሲ በልዩ ሁኔታ ሊታደስ ነው

 

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጂቡቲ የሚገኘውን ታሪካዊውን የኢትዮጵያን ኤምባሲ በልዩ ሁኔታ ለማደስ ስምምነት ተፈረመ።

ከስድስት አስርት ዓመታት በላይ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ታሪካዊ የቀድሞ ኤምባሲ ነው።

ከ1958 እስከ 1996ዓ.ም ድረስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና ቆንስላ ጽ/ቤት ሆኖ ሲያገለግል የቆየውን ህንጻ ታሪካዊ ይዘቱን ሳይለቅ የኢትዮጵያን ገጽታ በሚያስተዋውቅ መልኩ ልዩ ዕድሳት ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ሰነድ በጂቡቲ የኢትዩጵያ ኤምባሲ እና በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን መካከል በዛሬው ዕለት የተፈረመው።

በጂቡቲ የስራ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።

ለረጅም ጊዜ ስራ ሳይሰጥ ተዘግቶ የቆየውን ይሄንን የኢትዮጵያ ሃብት ታሪኩን በሚመጥን መልኩ በማደስ የገጽታ መገንቢያ እና ገቢ ማስገኛ ልዩ ስፍራ ለማድረግ እንዲቻል የዕድሳት ስራውን ለመጀመር ስምምነት መፈረሙ አንድ ስኬት ነው ብለዋል፡፡

በጂቡቲ የሚገኘው ሚሲዮን ከህንጻው በሚያገኘው ገቢ ራሱን የማስተዳደር አቅም የሚፈጥር ሲሆን፥ የመንግስትን የውጭ ምንዛሬ ወጪን ለመቀነስ ከፍተኛ ጥቅም እንደሚኖረው ጠቅሰዋል፡፡

ሰየተካሄዷልነ-ስርዓቱ በሚሲዮኑ መሪ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ተወካይ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው አማካኝነት ስለመካሄዱ ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.