Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ቡድን ህውሓት እታገልለታለሁ ለሚለው የትግራይ ህዝብ እንኳን ምንም ርህራህ የሌለው የአጥፊዎች ስብስብ ነው -የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ቲጃኒ ናስር

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በዛሬው ዕለት በጅማ ከተማ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ፣ የጁንታውን ሴጣናዊ ተግባር የሚያወግዝና የውጭ ሀገራትን ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ሰልፍ በጅማ ስቴዲየም ተካሂዷል፡፡
የጅማ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች የአሸባሪውን ቡድን ህውሓትን በማውገዝ፥ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ድጋፍና የታላቁ ህዳሴ ግድብ 2ኛ ዙር ውሃ ሙሌት እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል።
ሰልፈኞቹ የሀገራት ጣልቃ ገብነትም ተቀባይነት የለውም ነው ያሉት።
በጅማ ስቴዲየም እየተካሄደ በሚገኘው የድጋፍ መርሃ-ግብር ላይ÷ የኢትዮጵያ ፍላጎትና ምኞት ሠላም፣ አንድነት እና ብልፅግና ነው!ብለዋል።
በድጋፍ ሰልፉ ላይ ስለ ሀገር አንድነት የሚሰብኩ፣ የመከላከያ ሰራዊትን ለሀገር ሉዓላዊነት የሚከፍለውን መስዋትነት የሚያወድሱ፣ ሀገራት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት የሚኮንኑ መፈክሮች ተስተጋብተዋል፡፡
የጅማና አካባቢዋ ነዋሪዎችም ለሀገር ሰለምና ዕድገት አንድነታችን በማጠናከር ከውስጥም ከውጭም የተጋረጠብንን ችግሮች ለመመከት ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡
የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ቲጃኒ ናስር የጅማ ከተማና ዞን ነዋሪዎች በሁለት ዙር ለመከላከያ ሰራዊታችን ያደረጉት ድጋፍ ከጎን መቆማቸውን በተግባር ያሳየ ነው ብለዋል።
አሸባሪው ቡድን ህውሓት እታገልለታለሁ ለሚለው የትግራይ ህዝብ እንኳን ምንም ርህራህ የሌለው የአጥፊዎች ስብስብ ነው ሲሉ የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ቲጃኒ ናስር ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም ጁንታው ስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት እታገልለታሁ ለሚለው የትግራይ ህዝብ ምንም ያልጠቀመ ሲሆን ÷ አሁን ላይ ዕድሜያቸው ለውትድርና ያልደረሱ ህፃናትን ወደ ጦር አውድማ በመላክ ለህዝቡ ምንም ርህራሄ እንደሌለው በግልፅ አሳይቷል ነው ያሉት፡፡
የጅማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱልሃኪም ሙሉ በበኩላቸው÷ የውስጥም ሆነ የውጭ ጠላት መዘንጋት የሌለባቸው ምንም እንኳን ድሃ ብንሆንም በክብሩና በነፃነቱ የሚደራደር ኢትዮጵያዊ እንደሌለ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
አባቶቻችን በቀኝ ግዛት ያልተገዛች ሀገር አስረክበውን አልፈዋል እኛ ደግሞ ለተወሰኑ ቡድኖች ዕቅድ እጅ አንሰጥም ፣ ግብዓተ መሬታቸውን እናፋጥናለን እንጂ ብለዋል።
በተመስገን አለባቸው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
በተመስገን አለባቸው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+3
58,026
People Reached
3,215
Engagements
Boost Post
1.4K
40 Comments
63 Shares
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.