Fana: At a Speed of Life!

በፕሪምየር ሊጉ አራት ጨዋታዎች በመሸናነፍ ተጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በአዲስ አበበ እና በክልል ከተማዎች ተካሂደዋል፡፡

ፋሲለደስ ስታድየም ላይ ሲዳማ ቡናን ያስተናገደው ፋሲል ከነማ 1 ለ 0 በማሸነፍ በ18 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ መቀመጥ ችሏል፡፡

አዳማ ከተማ ሀድያ ሆሳዕናን አስተናግዶ 2 ለ 0 ያሸነፈ ሲሆን በዚህም በሁለት ነጥብ ልዩነት ከወራጅ ቀጠና መውጣት የቻለበትን ውጤት አስመዝግቧል፡፡

አዲስ አበባ ስታድየም ላይ ባህርዳር ከተማን ያስተናገደው ቅዱስ ጊዮርጊስ 1 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ሶስተኛ ደረጃ መጥቷል፡፡
በሌላ ጨዋታ አዲስ አዳጊው ወልቂጤ ከተማ ድሬዳዋ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፎ በተመሳሳይ በአንድ ነጥብ ልዩነት ከወራጅ ቀጠና መውጣት ችሏል፡፡

በሌላ ጨዋታ ወደ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ከኢትዮጵያ ቡና መቐለ ላይ ያደረጉት ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.