Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 30 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 14 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ለ4 ሺህ 352 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 30 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 22 ወንድ እና 8 ሴት ሲሆኑ፥ በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ናቸው።

ከዚህ ውስጥ 15ቱ በአዲስ አበባ፣ 2 ከትግራይ ክልል፣ 8 ከአማራ ክልል፣ 1 ሰው ከኦሮሚያ የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክም ሆነ ቫይረሱ ከተገኘበት ሰው ጋር ንክኪ የሌለው፣ 3 ሰዎች ከሐረሪ ክልል እንዲሁም 1 ሰው የድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪ መሆኑ ተገልጿል።

በአጠቃላይ ቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከል11ዱ የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆኑ 5ቱ ደግሞ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የነበራቸው ናቸው ተብሏል።

በአዲስ አበባ ደግሞ ቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከል ሁለቱ ቫይረሱ ካለበት ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው እና 13ቱ ደግሞ የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክም ሆነ ቫይረሱ ካለበት ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው መሆኑም ነው የተገለጸው።

በተያያዘም ትናንት ተጨማሪ 14 ሰዎች በአዲስ አበባ ከቫይረሱ ማገገማቸው ታውቋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.