Fana: At a Speed of Life!

አንደኛው ዙር የምክንያታዊ ወጣቶች ውይይት መድረክ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በብልጽግና ወጣቶች ሊግ አዘጋጅነት በሀገር ደረጃ በከተሞች እየተካሄደ ያለው አንደኛው ዙር የምክንያታዊ ወጣቶች ውይይት መድረክ ዛሬ በአፋር ሰመራ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ ምሁራን ወጣቶች እየተሳተፋበት ሲሆን የሀገረ መንግስት ግንባታና የወጣቱ ሚና በሚል ርዕስ የተሰናዳ ነው።

የሀገረ መንግስት ግንባታ ምንነት፣የኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደትና ትምህርት የሚወሰድባቸው ጉዳዮች፣የሌሎች ሀገራት የሀገረ መንግስት ግንባታ ልምዶች፣የሀገረ መንግስት ግንባታን እውን ማድረግ ይቻል ዘንድ የወጣቱ ሚና የሚሉ ነጥቦች ይዳሰሱበታል።

ሰላምና ብልጽግና የተረጋገጠባት፣ዜጎች በእኩልነት ተንቀሳቅሰውና ሰርተው ህይወታቸውን የሚመሩባትን ኢትዮጵያ ማጠናከር ይቻል ዘንድ ሀገረ መንግስቱ ሊቆምባቸው የሚገባው ምሰሶዎች እየተመከረበት ነው።

በመድረኩ የክልሉ አመራር እና ሌሎች እውቅ የፖለቲካ ሰዎች መሳተፋቸውን ከብልጽግና ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.