Fana: At a Speed of Life!

አየር ኃይል የህፃን ቢንያም ጌታቸውን የአብራሪነት ህልም እንዲሳካ አደርጋለሁ አለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ አየር ኃይል ÷ ህጻን ቢንያም ጌታቸው የሄሊኮፕተር አብራሪ የመሆን ህልሙን ለማሳካት ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የአየር ኃይሉ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ እና የጠቅላይ መምሪያው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ህጻን ቢንያም(አባቢያ) እና አሳዳጊ አክስቱን አነጋግረዋል፡፡

የጀግናው ወታደር ምክትል መቶ አለቃ ጌታቸው መሮዳ ልጅ ቢኒያም አባቱ በአሸባሪው ህወሃት ከበርካታ ወታደሮች ጋር በታገተበት ወቅት ብዙ መከራዎችን ከሠራዊቱ ጋር ያሳለፈ ልጅ ነው፡፡

ጀግናው ሰራዊታችን ከዕገታው ካስለቀቃቸው በኋላም የሄሊኮፕተር አብራሪ መሆን እንደሚፈልግ ለፋና ቴሌቪዥን ተናግሮ ነበር፡፡

አየር ኃይሉ ይህንን ራዕዩን ለማሳካት እንደሚሰራ የጠቆሙት ዋና አዛዡ ÷ህፃን ቢንያም ለጤና እና ትምህርት ስኬቱ ክትትል በማድረግ ዕድሜው ሲፈቅድ ደግሞ የአየር ኃይሉ አባል እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡

በዚህም ከአሁኑ ተገቢውን ክትትል በማድረግ የአየር ኃይል ጉብኝት እና የክህሎት ማሳደጊያ ሁኔታዎችን እንደሚመቻችለት ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለህፃን ቢንያም የመኖሪያ ቤትና የገንዘብ ስጦታ ማበርከታቸው ይታወሳል፡፡

በሶዶ ለማ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.