Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ ነገ ከንጋቱ 11፡30 ጀምሮ 125ኛውን የአድዋ ድል ታስባለች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 125ኛው የአድዋ ድል በዓል ነገ ከንጋቱ 11 ሰዓት 30 ጀምሮ በመዲናዋ  እንደሚከበር የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አስታወቁ፡፡

ምክትል ከንቲባዋ በማህበራዊ ገጻቸው እንዳስታወቁት ከንጋት ጀምሮ ከአራቱም የከተማው አቅጣጫዎች ከሚመጡ ተሳታፊዎች ጋር የድል በዓሉን ለማክበር ዝግጅታችንን አጠናቀናል ብለዋል፡፡

ምክትል ከንቲባዋ የኢትዮጵያዊነት ልዕልና ፣ የትላንት ደማቅ ታሪክ፣ የዛሬ ትውልድ ወኔ እና የነገ ተተኪዎች ስንቅ ለሆነው የአድዋ ድል 125ኛ ዓመት ክብረ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

የአድዋ ዘማቾች መሰባሰቢያና መነሻ በሆነችው አዲስ አበባ ላይ ከባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የጥቁር ህዝቦች ኩራት የሆነው የአድዋ ድል በዓል  በደመቀ ሁኔታ እንደሚከበርም ነው ያስታወቁት::

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.