Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ የ600 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ጋር የ600 ሚሊየን ዶላር የድጋፍና የብድር ስምምነት ተፈራረመ።
ከ600 ሚሊየን ዶላር ውስጥም 200 ሚሊየን ዶላሩ በድጋፍ መልክ ሲሆን፥ 400 ሚሊየን ዶላሩ በብድር መልክ ነው።
ስምምነቱ በኢትዮጵያ ያለውን የስርአተ ምግብ ለማሻሻል እና የምግብ እጥረት አደጋን ለመቀነስ የሚውል መሆኑ ተገልጿል።
ገንዘቡ የምግብ እጥረት አለባቸው ተብለው በተለዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የምግብ እጥረት አደጋን ለመቀነስ ብሎም የስርአተ ምግብን ለማሻሻል የሚውል ይሆናል።
ከዚህ ባለፈም የአርብቶ አደሮችን የኢኮኖሚ ልማት በማሳደግ የድርቅ ተጋላጭነታቸውን ለመቀነስ እንደሚውል የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.