Fana: At a Speed of Life!

ከአሸባሪው ህወሓት ወረራ ነጻ በወጡ አካባቢዎች የሚገኙ ሆስፒታሎች ሥራ እንዲጀምሩ የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአሸባሪው ህወሓት ወረራ ነጻ በወጡ አካባቢዎች የሚገኙ ሆስፒታሎችን መልሶ ለማደራጀት እና ወደ መደበኛ ሥራ ለማስገባት ግብዓት እየተሰባሰበ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ገለፀ።

ከተማ አስተዳደሩ በመቄት ወረዳ አሸባሪው ቡድን ላወደመው የሸድሆ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የመድኃኒት እና የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

አሸባሪው የህወሓት ወራሪ ቡድን በሸድሆ መቄት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ላይ ከ35 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ፣ መድኃኒት እና ትላልቅ ማሽኖችን ዘርፏል፤ መውሰድ ያልቻለውንም አውድሟል።

ተቋሙ በደረሰበት ከፍተኛ ዝርፊያ እና ውድመት ምክንያትም ለወራት የህክምና አገልግሎት ተስተጓጉሎ መቆየቱ የተገለጸ ሲሆን፥ በዚህም ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች በርካታ ናቸው ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ የሆስፒታሉን የህክምና አገልግሎት ዳግም ማስጀመር የሚያስችል የመጀመሪያ የመድኃኒት እና የህክምና መሣሪያዎች ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉ የተደረገው በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ሁሉንም ሆስፒታሎች፣ መድኃኒት ቤቶችን እና የቢሮው ሠራተኞችን በማስተባበር መሆኑም ነውየተገለጸው።

የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ምክትል ኀላፊ ዶክተር ሙሉጌታ እንዳለ፥ 1 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ልዩ ልዩ መድኃኒቶች እና የህክምና መሣሪያዎችን አስረክበዋል።

‟ብዙ የጤና ተቋማት መውደማቸውን በአካል ተገኝተን ተመልክተናል“ ያሉት ዶክተር ሙሉጌታ፥ በቀጣይም በሚለቀቁ አካባቢዎች ሆስፒታሎችን መልሶ ማደራጀት እና ወደ መደበኛ ሥራ ማስገባት የሚያስችል ግብዓት የማሰባሰብ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ማመልከታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.