Fana: At a Speed of Life!

ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በቤንች ሸኮ ዞን ከህብረተሰቡ ጋር እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት እያደረጉ ነው።

በውይይት መድረኩ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ፍሬዓለም ሽባባው፣ የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም ጄነራል አደም መሐመድ፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል እንዳሻው ጣሰው፣ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው እና ሌሎችም የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በውይይቱ ሰሞኑን በአካባቢው በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችና ሌሎችም የማህበረሰብ ተወካዮች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.