Fana: At a Speed of Life!

ዋልያዎቹ የመጀመሪያ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ነሐሴ 28 ያከናውናሉ

 

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎችን የሚያደርግባቸው ቀናት ታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በኳታር አስተናጋጅነት ለሚካሄደው 2022 የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ 7 ከጋና፣ዚምቧቡዌ እና ደቡብ አፍሪካ ጋር መደልደሉ ይታወቃል።

ዋልያዎቹ የመጀመሪያ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ከጋና ጋር አክራ ላይ ነሐሴ 28፣2013 የሚያከናውኑ ሲሆን 2ኛ ጨዋታቸውን በባሕር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም ጳጉሜ 2፣2013 ዚምቧቤን ይገጥማሉ።

የአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ስብስብ በአዳማ ኤክስኪዪቲቭ ሆቴል መቀመጫውን በማድረግ ዝግጅቱን ከጀምረ ሳምንታት ማስቆጠሩን ከኢትዩጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በበተያያዘ ዜና ብሔራዊ ቡድኑ ከዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች በፊት ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎችን ያደርጋል።

የመጀመሪያ የወዳጅነት ጨዋታውን ከሴራሊዮን ብሔራዊ ቡድን ጋር፣ ሁለተኛውን ከዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን ጋር ነሐሴ 20፣2013 እና ነሐሴ 23፣2013ዓ የሚያካሂድ ይሆናል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.