Fana: At a Speed of Life!

የህወሓት ቡድን ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ ህገ-ወጥ ተግባር ፈፅሟል – አፈ-ጉባኤ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ህወሓት ቡድን ከሃገራዊ ለውጡ በፊትና በኋላ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ ክልላዊ ምርጫን ጨምሮ የተለያዩ ህገ-ወጥ ተግባር መፈፀሙን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አደም ፋራህ ገለጹ።

አፈ ጉባኤው ዛሬ በሰጡት መግለጫ ቡድኑ ህገወጥ ድርጊቱን እንዲያቆም በምክር ቤቱ ተደጋጋሚ ጥሪ ቢደረግለትም ህገ-መንግስቱን አደጋ ላይ የሚጥሉ ድርጊቶችን ከማድረግ ሊቆጠብ አልቻለም ነበር ብለዋል።

ይህን ተከትሎም የህወሓት ምክር ቤት እንዲፈርስ ስራ አስፈጻሚው አካልም ዕውቅና እንዳይኖረው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ማሳለፉን አስታውሰዋል።

በክልሉም ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ምክር ቤቱ መወሰኑና ውሳኔው ህገ-መንግስቱን ለማስፈጸም የወጣውን አዋጅ ቁጥር 359/95 መሰረት በማድረግ ነው ብለዋል።

መንግስት ይህን ቡድን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል የወሰደው እርምጃ የንጹሃን ዜጎችን ደህንነት በጠበቀ መልኩ መሆኑንም ገልጸዋል።

የህግ ማስከበር ዘመቻው በህገ- መንግስቱ መሰረት በብቃትና በውጤታማነት መፈጸሙንም ምክር ቤቱ ገምግሟል ብለዋል አፈ ጉባኤው።

ምክር ቤቱ በቀጣይም በትግራይ ክልል የሚከናወኑ ተግባራት በህገ -መንግስቱ መሰረት መፈጸም አለመፈጸማቸውን እንደሚከታተል አስረድተዋል።

በዚህ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በክልሉ ስላለው ሁኔታ በቀጣይ ለምክር ቤቱ ሪፖርት ያቀርባሉም ነው ያሉት።

በክልሉ የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር የክልሉ ከፍተኛ የህግ አስፈጻሚ አካል የነበሩት ስልጣንና ተግባር የሚኖሩት በመሆኑ የክልሉን እቅድና በጀት ያጸድቃል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ በይፋ ስራውን መጀመሩን ተከትሎ በከተሞችና ወረዳዎች የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በሚያሳትፍ መልኩ አመራሮችን መመደቡ ጥሩ ጅምር መሆኑንም አፈ ጉባኤው መግለጻቸውን ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.