Fana: At a Speed of Life!

የህወሓት ቡድን ሲጠቀምበት የነበረ 32 ኩንታል አደንዛዥ እፅ ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህወሓት ቡድን ሲጠቀምበት የነበረ 32 ኩንታል አደንዛዥ እፅ ተያዘ፡፡

አደንዛዥ እፁ በተሽከርካሪ ተጭኖ ከሁመራ ወደ የተለያዩ አካባቢዎች ሊገባ ሲል መያዙን የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ቴዎድሮስ ብርጌድ ዋና አዛዥ ኮማንደር ዘለቀ ምትኩ ለአብመድ ተናግረዋል፡፡

በዓለም አቀፍ ህግ የተከለከለውን ካናቢስ የተሰኘውን እፅ የህወሓት ዘራፊ ቡድን እድሜያቸው ለጦርነት ያልደረሱ ህፃናት እንዲጠቀሙት በማድረግ ወደ ጦርነት እያስገባቸው መሆኑን እጃቸውን የሰጡ የቡድኑ የልዩ ኃይል አባላት መናገራቸውን ዋና አዛዡ ገልጸዋል፡፡

ዘራፊ ቡድኑ ህፃናትን ወደ ጦርነት ማስገባቱ ሳያንሰው ዓለም አቀፍ ወንጀል የሆነውን አደንዛዥ ዕፅ ህፃናት እንዲጠቀሙበት ማድረጉ የወረደ ተግባር ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

ከአደንዛዥ እፁ በተጨማሪ ህገወጡ ህወሓት በአልመዳ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ያመረታቸው የፌደራል ፖሊስ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የማረሚያ ቤት ፖሊስ አልባሳት አብረው መያዛቻውንም ነው የተናገሩት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.