Fana: At a Speed of Life!

የመሰረታዊ ሸቀጦች አቅርቦት እና ስርጭት ላይ  የመረጃ ፍሰት ስርዓት ግምገማ ዓውደ ጥናት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 10፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና በማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ የጋራ ትብብር የተዘጋጀ የመረጃ ፍሰት ስርዓት ግምገማ ዓውደ ጥናት በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል ፡፡

ዓውደ ጥናቱ የመሰረታዊ ሸቀጦች አቅርቦትና ስርጭት ላይ የሁለቱ ተቋማት የአሰራር ሂደት በፌደራልና በክልል ያለውን የመረጃ ቅብብሎሽ ላይ  ትኩረት ማድረጉ ተገልጿል፡፡

የፌዴራል ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ አዳማ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ደበበ ወዳጆ÷  አውደ ጥናቱን በይፋ ሲከፍቱ መረጃ በጥናት እና በተቀናጀ የአሰራር ስርዓት ለህብረተሰቡ ለማቅረብ በቅንጅት መስራት አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

እንደ ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ የሪፖርት አሰባሰብ፣ የጥናት ሂደት እና መረጃን በተቀናጀ አሰራር መስራት የስታቲስቲክሱን ስርዓት ምቹ ያደርገዋልም ነው ያሉት፡፡

ስለዚህ ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እንዲሁም መረጃ የሚያመነጩትን ክልሎች እና ከተማ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊዎች በተገኙበት፣ በጋራ እና  በመተባበር በአቅም ግንባታ ስልጠና እና ቴክኒካል ድጋፍ በማድረግ የተጠናከረ የመረጃ ፍሰት እንዲኖር  አውደ ጥናቱ ያግዛል ሲሉ ገልጸዋል ፡፡

በአውደ ጥናቱ የክልል እና የከተማ አስተዳደር የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ  ኃላፊዎች፣ የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ እና የተቋሙ የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች መሳተፋቸውን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.