Fana: At a Speed of Life!

የመቐለ ከተማ የንግዱ ማህበረሰብ 15 አባላት ያሉት የመማክርት ኮሚቴ አቋቋመ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመቐለ ከተማ የሚገኙ የንግድ ማህበረሰብ አባላት በዛሬው እለት ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ውይይት አድርገዋል።
 
በዚሁ ውይይት ላይም የንግዱ ማህበረሰብ 15 አባላት ያሉት መማክርት ኮሚቴ ማቋቋማቸው ተገልጿል።
 
ይህ ኮሚቴም በነገው ዕለት ተሰብስቦ የራሱን አመራሮች እንደሚመርጥ ታውቋል።
 
የንግዱ ማህበረሰብ በዛሬው ውይይት ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን÷ በዋናነትም በከተማዋ ያለው የፀጥታና የማረጋጋት ስራ በትኩረት እንዲሰራ መጠየቃቸው ተገልጿል፡፡
 
አሁን ላይ በከተማዋ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑ የሚያስመሰግን መሆኑን የጠቀሱት ነጋዴዎቹ በተመሳሳይ የግል ባንኮችም ስራ እንዲጀምሩ ጥያቄ አቅርበዋል።
 
ከገንዘብ ቅያሬው ጋር በተያያዘ በክልሉ በነበረው የህግ ማስከበር ዘመቻ ምክንያት ቀላል የማይባል ቁጥር ያለው የንግዱ ማህበረሰብ በእጁ ላይ ያለውን ገንዘብ መቀየር ባለመቻሉ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ለዚህ ችግር መፍትሄ እንዲሰጣቸውም መጠየቃቸውም ተገልጿል፡፡
 
በከተማዋ አሁን ላይ መደበኛ የትራፊክ ፖሊስ እና የታክሲ አገልግሎት ስራ የጀመረ ሲሆን÷ ከዚህ በፊት ከፍተኛ የታሪፍ ጭማሪ አድርገው የነበሩ ታክሲዎችም ወደ መደበኛ ታሪፍ እንደተመለሱና በመደበኛ መስመር ላይ ስራቸውን እያከናወኑ መሆኑንም የከተማውን ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ጠቅሶ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.