Fana: At a Speed of Life!

የሳይንስ ካፌዎች ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ ሚኒስቴሩ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የሳይንስ ካፌ ማዕከላት ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ ተገቢው ክትትል እንዲደረግ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡
በተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት የተዘጋጀ የፓናል ውይይትና የሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ አውደ ርዕይ በባሕርዳር ከተማ ተከፍቷል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር÷ ቀጣይነት ያለው ልማት ለማረጋገጥ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዕውቀት የተደገፉ አምራች እና ሳይንሳዊ አስተሳሰብ ያለው ዜጋ መፍጠር መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ግንዛቤና ባህል በህብረተሰቡ ውስጥ እንዲዳብር የሳይንስ ካፌዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው÷ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የሳይንስ ካፌ ማዕከላት ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ አሳስበዋል።
የሳይንስ ካፌዎች ህብረተሰቡን÷ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ጉዳዮች ግንዛቤውን እንዲያዳብር የሚሠራባቸው፣ ሥልጠናዎች የሚሰጡባቸው፣ የሥራ ፈጠራ ሃሳብ የሚጠነሰሱባቸው፣ ማንበቢያና የፈጠራ ሃሳብ የሚዳብሩበት እንዲሁም የፈጠራ ባህል ማጎልበቻ ማዕከላት መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡
ስለሆነም ማዕከላቱ ከትምህርት፣ ከምርምር እና ከቴክኖሎጂ ዘርፍ ተቋማት ጋር በቅርበት እንዲሠሩ ለማድረግ መሰል መድረኮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ አውደ ርዕዩ÷ በፖሊሲዎች እና ስትራቴጂዎች ላይ ውይይት እንደሚደረግበት እና ኤግዚቪሽን፣ የኢኖቬሽን ስነ ምህዳር ስልጠና እና የፓናል ውይይቶች ይደረጉበታል፡፡
ለሁለት ቀናት በሚቆየው አውደ ርዕይ ላይ÷ ከ2007 እስከ 2014 የተሠሩ የፈጠራ ሥራዎች እንደሚቀርቡ የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.