Fana: At a Speed of Life!

የብሄራዊ የኮቪድ19 መከላከልና መቆጣጠር የሚኒስቴሮች ኮሚቴ ከክልሎችና ከተማ መስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት አካሄደ

አዲስ አበባ ፣ግንቦት 27 ፣2012 ፣ (ኤፍ.ቢ.ሲ) የብሄራዊ የኮቪድ19 መከላከልና መቆጣጠር የሚኒስቴሮች ኮሚቴ ዛሬ ከክልል ርዕሳነ መስተዳድሮችና ከከተማ መስተዳድር ከፍተኛ አመራሮች ጋር በወረርሽኙ ስርጭት መስፋፋትና መከላከል  ዙሪያ ውይይት አካሄደ።

ከዚያም ባለፈ በውይይቱ የወረርሽኙን ስርጭት ለመቀነስና ለመከላከል እየተደረጉ ባሉ ተግባራት  ተግባራት ላይ  ላጋጠሙ  ችግሮች የመፍትሄ አቅጣጫ ተቀምጧል ።

በሀገራችን የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ቢሄድም ህብረተሰቡ አሁንም በከፍተኛ ደረጃ መዘናጋት እንደሚታይበት  በውይይቱ ወቅት ተገምግሟል።

ስለሆነም የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸዉና የተከለከሉና አስገዳጅ ሁነቶች ላይ የተጠናከረ ህግ የማስከበር ሂደት እንዲቀጥል አቅጣጫ  መቀመጡም ነው የተገለጸው።

የቫይረሱ ስርጭት በመደበኛዉ የህክምና አገልግሎት ላይ ያሉ ባለሙያዎችንም ጭምር እያጠቃ በመሆኑ በህክምና መስጫ ስፍራዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ መወሰድ እንዳለበትና የመከላከያ ግብአቶችም በትኩረት መዳረስ እንዳለባቸው አቅጣጫ ተቀምጧል።

ከዚያም ባለፈ በውይይቱ በድንበር አካባቢ ስርጭቱን የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባራት እንዲሁም የማቆያ ቦታዎች አስተዳደር መሻሻል ቢያሳይም አሁንም ጠንካራ ቁጥጥርና ክትትል እንደሚያስፈልግ አፅንኦት መሰጠቱን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.