Fana: At a Speed of Life!

የቱርሚ-ኦሞ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ 48 ኪሎ ሜትሩ የአስፋልት ግንባታ ስራ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቱርሚ-ኦሞ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ 48 ኪሎ ሜትሩ የአስፋልት ግንባታ ስራ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
57 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው መንገድ በመፋጠን ላይ ሲሆን ÷ ቀሪ የግንባታ ክፍሉን በጥራት ገንብቶ ለማጠናቀቅም በትኩረት እየተሰራ ነው ተብሏል።
ስራውን ለማካሄድ የተመደበው 897 ሚሊየን ብር በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ሲሆን ÷ግንባታውን በማካሄድ ላይ የሚገኘው ራማ ኮንስትራክሽን የተባለ ሀገር በቀል የስራ ተቋራጭ ድርጅት ነው፡፡
ፕሮጀክቱን የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ደግሞ ስታዲያ ኢንጂነሪንግ ወርክስ ኮንሰልታንት የተባለ ሀገር በቀል አማካሪ ድርጅት በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
መንገዱ ሲጠናቀቅ በደቡብ ክልል ውስጥ የምትገኘውን ቱርሚ ከተማን ከካንጋቴን ከተማ ጋር በማስተሳሰር የነበረውን የትራንስፖርት የመሰረተ ልማት ችግር እንደሚፈታ ተገልጿል።
እንዲሁም በአካባቢው ለሚገኙ ትንንሽ ከተሞች ዕድገት የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡
የዚሁ የመንገድ አካል ትስስር የሆነው የወይጦ ቱርሚ መስመርን በአስፋልት ደረጃ ግንባታውን ለማካሄድ የጨረታ ሂደቱ በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን ÷በያዝነው አመትም ወደ ግንባታ ስራ እንደሚሸጋገር ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.