Fana: At a Speed of Life!

የቱርክ ባለሃብቶች በተመረጡ የማዕድን ሃብቶች ላይ በሰፊው እንዲሳተፉ መግባባት ላይ ደርሰናል – ኢ/ር ታከለ ኡማ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱርክ ባለሃብቶች በተመረጡ የማዕድን ሃብቶች ላይ በሰፊው እንዲሳተፉና በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ ደርሰናል ሲሉ የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገለጹ፡፡
 
ኢንጂነር ታከለ ኡማ በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ያብራክ አልፕ ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
በውይይታቸውም፥ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቱርክ ቆይታቸው ወቅት የሁለቱን ሀገራት ስትራቴጂክ አጋርነት ለማጠናከር በተፈራረሙት የተለያዩ ስምምነቶች ላይ ያተኮረ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
 
ከዚህ ባለፈም የቱርክ ባለሃብቶች በማዕድን ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት ላይ በሚሳተፉበት እድል ዙሪያ ሰፊና ገንቢ ምክክር ማድረጋቸውን ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
 
በተለይም የቱርክ ባለሃብቶች በተመረጡ የማዕድን ሃብቶች ላይ በሰፊው እንዲሳተፉና በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ መደረሱን ነው የገለጹት፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.