Fana: At a Speed of Life!

የቻይናና አፍሪካን አጋርነት የሚያጠናክር ሲምፖዚየም ቤጂንግ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና እና አፍሪካን አጋርነት የሚያጠናክር ሲምፖዚየም ቤጂንግ በሚገኘው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ተካሄደ፡፡
ሲምፖዚየሙ ቻይና የሚገኙ የአፍሪካ አምባሳደሮች ቡድን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጽህፈት ቤት በመተባበር ነው የተዘጋጀው።
የአፍሪካን እና ቻይናን የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በማለም የተዘጋጀው ሲምፖዚየሙ፥ ቀደም ሲል በሴኔጋል ዳካር በተካሄደው የሁለቱ ወገኖች የሚኒስትሮች ኮንፈረንስ ላይ የተወሰኑ ውሳኔዎችን ተግባራዊ ማድረግ ላይ አተኩሮ መካሄዱ ተጠቅሷል።
በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ የቻይናና አፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች ኮንፈረንስ ውጤቶችን በተመለከተ የነበረውን ጠቃሚ ውይይት የመሩ ሲሆን፥ በውይይቱም ወቅት ስለ ጤና፣ ስለ ኮንፍረንሱ ውሳኔዎች አፈጻጸም እና ሌሎች አህጉሪቷን የተመለከቱ ጉዳዮች ተነስተዋል።
ለአንድ ቀን በቆየው ሲምፖዚየም ላይ በቻይና-አፍሪካ የትብብር ማእቀፍ ውስጥ የአካባቢ ጥበቃ፣ የገጠር ልማት፣ የማህበረሰብ ጤና፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን መከላከል፣ ፋይናንስና ኢንቨስትመንትን ባካተቱ አጀንዳዎች ላይ ውይይት መደረጉን ነው ኤምባሲው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መረጃ የጠቆመው።
በቻይና የሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች፣ በቤጂንግ ተቀማጭ የሆኑ የተመድ የሥራ ሀላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች እና የቻይና የመንግስት ምክር ቤት እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቤት የሥራ ሀላፊዎች በሲምፖዚየሙ ላይ ተሳትፈዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፤ እንገንባ፤ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.