Fana: At a Speed of Life!

የቻይና ተመራማሪዎች ኮሮና ቫይረስን በ15 ደቂቃ ውስጥ መለየት የሚችል መሳሪያ ይፋ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይና ተመራማሪዎች ኮሮና ቫይረስን በ15 ደቂቃ ውስጥ መለየት የሚያስችል መሳሪያ ይፋ አደረጉ።

መሳሪያው በመተንፈሻ አካላት የህክምና ባለሙያዎች አማካኝነት ነው ሙከራ የተደረገለት።

ቫይረሱን ከመለየት ባሻገርም በተለያየ ደረጃ ያሉ የቫይረሱን ተጠቂዎች ሁኔታ መለየት ይችላልም ነው የተባለው።

ተመራማሪዎቹ ከ397 የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች የተሰበሰቡ ናሙናዎችን በመጠቀም ሙከራውን አድርገዋል።

በዚህም አዲሱ መሳሪያ ቫይረሱን የማረጋገጥ አቅሙ 88 ነጥብ 66 በመቶ ሆኗል።

ከዚህ ባለፈም የመለየት አቅሙ ደግሞ 90 ነጥብ 63 በመቶ ሆኗልም ነው ያሉት ተመራማሪዎቹ።

መሳሪያው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን በፍጥነት ለመለየት ለሚደረግ ጥረት አጋዥ መሆኑንም ገልጸዋል።

 

ምንጭ፦ ሲ ጂ ቲ ኤን

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.