Fana: At a Speed of Life!

የአሸባሪው ሸኔ የጥፋት ድርጊትን ለመመከት የበኩላችንን እየተወጣን ነው – ወጣቶች

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ሸኔ በሰውና ንብረት ላይ የሚፈጽመውን የጥፋት ድርጊት ለመመከት የበኩላቸውን እየተወጡ መሆናቸውን በምዕራብ ወለጋ ዞን አስተያየታቸውን የሰጡ ወጣቶች ገለጹ።

ወጣቶቹ የአሸባሪ ቡድኑን አስነዋሪ ተግባር ለማስቆም ከመንግስት ጎን እንደሚቆሙ ነው ያመለከቱት።

ቡድኑ አሁን ላይ ተስፋ በመቁረጥ ሰዎችን ጭካኔ በተሞላበት መንገድ እየገደለና መሰረተ ልማቶችን እያወደመ መሆኑ እንዳስቆጣቸው በመግለጽ የጥፋት ድርጊቱን አውግዘዋል፡፡

በመንግስትና ህዝብ ገንዘብ፣ ጉልበትና እውቀት ተሳትፎ የተገነቡ መሰረተ ልማቶችን እያፈረሰ ጭምር መቀጠል ስለሌለበት የጥፋት ተግባርን በመመከት ለማስቆም ከፀጥታ አካል ጋር በመሆን የበኩላቸውን እየተወጡ መሆኑን ነው ያመላከቱት።

የምዕራብ ወለጋ ዞን የአስተዳደርና የፀጥታ ጽህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ ሙላቱ ዲንሳ በበኩላቸው፥ አሸባሪው ሸኔ በዜጎች ላይ እያደረሰ ያለው ግፍና መከራ ተቀምጠን የምናይበት ጊዜ አይደለም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በዞኑ አንዳንድ አካባቢዎች የሽብር ቡድኑን እንቅስቃሴን በመከታተል ለጸጥታ አካል መረጃ በመስጠት በተለይ ወጣቶች እያደረጉት ያለው ድጋፍ የሚበረታታ መሆኑን ገልጸው ወደ ህግ እንዲቀርቡ የበኩላቸውን እየተወጡ እንደሚገኙም አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.