Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ አዲስ ዓመቷን ተቀብላለች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የራሷን የቀን አቆጣጠር የምትከተለው ኢትዮጵያ አዲስ ዓመቷን ተቀብላለች።

የ2013 አዲስ ዓመትን በማስመልከት በተለይም በአዲስ አበባ ደማቅ የዋዜማ በዓል በይፋ በተመረቀው ሸገር ፓርክ የወዳኝነት አደባባይ በድምቀት ተከናውኗል።

በዚህ የዋዜማ ዝግጅት ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የፌደራልና የክልል የስራ ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የዋዜማ በዓሉ የተከበረበት የወዳጅነት አደባባይ በተለያዩ ደማቅ እና ሀብረ ቀለማት ባላቸው መብራቶች እና የውሃ ትርኢት የደመቀ ሲሆን፥ ይህም ለዋዜማ በዓሉ ልዩ ድባብ ሰጥቷል።

እንዲሁም የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች ጥዑመ ዜማዎች እና በስተመጨረሻ የነበረው የርችት ተኩስ ስነ ስርዓት ሌሎቹ በዓሉን ያደመቁ ሁነቶች ነበሩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.