Fana: At a Speed of Life!

የአድዋ ድል በዓል በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የ125ኛው የአድዋ ድል በዓል በደቡብ ክልል ደረጃ በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ተከበረ፡፡

በዓሉ በደቡብ ክልል ደረጃ  በሶዶ ከተማ የተለያዩ የክልልና የዞን  የሥራ ሀላፊዎች፤አባት አርበኞችና ሌሎችም ታድመዋል፡፡

በዓሉን ለተሳፉ እንግዶች  የእንኳን ደህና መጣችሁ  የመክፈቻ  ንግግር  ያደረጉት  የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ  ዶክተር  እንድሪያስ  ጌታ  የአድዋ በዓል በሀገር ሉዓላዊነት ላይ የተቃጣ ሴራ የከሸፈበት እንዲሁም በጥቁር ህዝቦች ታሪክ ኢትዮጵያ ታላቅ ድል የተጎናፀፈችበት የድል  በዓል ነው ብለዋል፡፡

የደቡብ ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀይለማሪያም ተስፋዬ አድዋ የህብረ-ብሔራዊነታችን ማህደር የነፃነታችን ዓርማ በመሆኑ ወጣቱ ትዉልድ አወቆትና ተረድቶት ሊያከብር እንደሚገባ ተናግረዋል:: በበዓሉ  አድዋን  የሚዘክሩ ጥናታዊ  ፅሁፎችና የሥነጽሑፍ ሥራዎች ቀርበዋል፡፡

በኢብራሂም ባዲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.