Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን ከወትሮው በላቀ አገልግሎት ማስተናገድ ያስፈልጋል- አምባሳደር ብርቱካን አያኖ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2014 (ኤፍ. ቢ.ሲ) 35ኛውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤና 40ኛውን የአስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባ ቅድመ ዝግጅት በተመለከተ የብሔራዊ የዝግጅት ኮሚቴ አባላት የተሳተፉበት ውይይት ተካሂዷል።
በወቅቱም ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅድመ ዝግጅቱ ላይ የተዘጋጀውን እቅድ መነሻ በማድረግ ምክክር ተደርጎበታል።
ውይይቱን የመሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታአምባሳደር ብርቱካን አያኖ፥ ሀገራችን በተለይ በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ የመሪዎችን ጉባኤና የአስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባን እንድታካሂድ እድል ማግኘቷ ትልቅ ስኬት በመሆኑ ከወትሮው በተለየ መልኩ በላቀ አገልግሎትና ቀልጠፋ መስተንግዶ እንግዶቹን መቀበል እንደሚገባ ተናግረዋል።
ኮቪድ-19 ከተከሰተ በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ በአካል የሚካሄድ የመሪዎች ጉባኤ መሆኑን ያስታወሱት ሚኒስትር ዴኤታዋ፥ ኢትዮጵያ በውስጥ ጉዳይዋ ያጋጠማትን ችግር ተከትሎ የተከፈተባትን ገፅታ የማጠልሸት ተግባር ስህተት መሆኑን የምናሳይበት መልካም አጋጣሚ በመሆኑ ጠንካራ የቅንጅት ስራዎችን ማከናወን አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
በውይይቱም የብሄራዊው ኮሚቴ መስርያ ቤቶች ተግባራትና ሀላፊነቶች በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።
በዚህም ከአውሮፕላን ማረፊያ ጀምሮ አጠቃላይ እስከ ቆይታ ጊዜያቸው ድረስ እንግዶች ምንም አይነት የደህንነት እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች እንዳይገጥማቸው መደረግ ባሉባቸው ዝግጅቶችን በተመለከተ ሀሳብ ቀርቦ ምክክር ተካሂዶባቸዋል።
ብሄራዊ ኮሚቴው በሁሉም ረገድ የተቀናጀ ስራ በመስራትና አፍሪካዊ ትስስርን የሚያጎሉ መስተንግዶዎችን በማድረግ የኢትዮጵያ መልካም ገፅታ ማሳየት እንደሚገባም መጠቆሙን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጥህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፤ እንገንባ፤ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.