Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ልማት ኤጀንሲ በይፋ ስራ መጀመሩን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ልማት ኤጀንሲ በይፋ ስራ መጀመሩን አስታውቋል፡፡

ኤጀንሲው በሰጠው መግለጫ የፋይናንስ ዘርፉ በኢትዮጵያ ተደራሽ፣ አካታች እና ዘላቂ የሆኑ የፋይናንስ ገበያዎችን ለማሳደግ እንዲሁም የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣት እንደሚሰራ ገልጿል፡፡

በተጨማሪም ኤጀንሲው የገበያ ስርዓት ዘዴዎችን በመጠቀም በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ስርዓት ለውጥን ያበረታታል ተብሏል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ፥ ድርጅቱ በፋይናንስ ስርዓቱ ላይ የተጋረጡ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚያበረታቱ ተናግረዋል።

በተለይም የፋይናንስ ገበያዎችን ይበልጥ ተደራሽ፣ አካታች እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ለመፍጠር በሚያስችል መልኩ ጠንካራ እንዲሆኑ ለማድረግ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፋይናንስ ዘርፍ ልማት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ኤርሚያስ እሸቱ በበኩላቸው፥ መንግስት የሃገሪቱን ዕድገት አካታች መሆኑን ለማረጋገጥ እንዲሁም የዕድገት ግቦችን ለማሳካት ኤጀንሲው የራሱን አስተዋፅኦ ያደርጋል ብለዋል፡፡

በምንይችል አዘዘው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.