Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 27፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ይካሄዳሉ።

የፕሪሚየር ሊጉ 2ኛ ዙር ከሁለት ሳምንታት እረፍት በኋላ ነገ እና ከነገ በስቲያ ቀጥሎ የሚካሄድ ይሆናል።

ቅዳሜ ኢትዮጵያ ቡና ከስሁል ሽረ እንዲሁም ፋሲል ከነማ ከአዳማ ከተማ ይጫወታሉ።

እሁድ የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልቂጤ ከተማን ያስተናግዳል።

ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከሰበታ ከተማ፣ ሲዳማ ቡና ከወላይታ ዲቻ፣ ሀዲያ ሆሳዕና ከመቐለ 70 እንደርታ፣ ባህርዳር ከተማ ከጅማ አባ ጅፋር እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ ከሀዋሳ ከተማ ይገናኛሉ።

ፕሪሚየር ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ28 ነጥብ ሲመራ፥ ፋሲል ከነማ በ26 መቐለ 70 እንደርታ በ25 ነጥቦች ይከተላሉ።

ድሬዳዋ ከተማ፣ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ሀዲያ ሆሳዕና በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ ይገኛሉ።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.