Fana: At a Speed of Life!

የኮምፒውተሮችን ደህንነት መጠበቅ የሚያስችሉ ዘዴዎች

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚጠቀሙባቸው ኮምፒውተሮች ከአገልግሎት ጋር ተያይዞ ለተለያዩ ውስጣዊና ውጫዊ ጥቃቶች የመጋለጥ እድላቸው ሰፊ ነው።

የኮምፒውተሮችን አጠቃላይ ባህሪ መረዳት፣ በየጊዜው ማሻሻልና መቀየር ያለባቸውን ስርዓቶች በማወቅ መረጃዎች እንዳይጠፉ ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።

ከዚህ አንጻር የኮምፒውተሮችን ደህንነት ለመጠበቅ

.ጠቃሚ ፋይሎችን መጠባበቂያ ወይም ባክአፕ መያዝ

. የኮምፒውተር ፕሮግራሞች ሥርዓት ለደህንነት ሥጋት እንዳይጋለጡ የኦፕሬቲንግ ሲስተም ክፍተት መሙላት

. ፀረ ቫይረስ ሶፍትዌሮችን መጠቀም፣ በየጊዜው መተግበሪያዎችን ማዘመን

. ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ አጠቃላይ የኮምፒውተር ስርዓት ስካን ማድረግ

.አጥፊ ሶፍትዌሮችን የሚከላከሉ ፀረ አጥፊ ሶፍትዌሮችን መጠቀም እና ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ ስካን ማድረግ እንዲሁም

. የተመጠነ የፋይል አስተዳደር መተግበር እና ዲስኮችን በየጊዜው ማፅዳት

መረጃው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ነው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.