Fana: At a Speed of Life!

የዜጎችን አንድነትና ወንድማማችነት ማስጠበቅ  የሁሉም ሀላፊነት ነው-የሶማሌ ክልል የሰላምና አንድነት መድረክ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዜጎችን አንድነትና ወንድማማችነት ማስጠበቅ የሁሉም ሀላፊነት መሆኑን እና የክልሉንም ሆነ የሀገሪቱን ሰላምና ፀጥታ ለማወክ የሚንቀሳቀሱ አካላትና ኃይሎች ከተግባራቸው እንዲቆጠቡ የሶማሌ ክልል የሰላምና አንድነት መድረክ ጥሪ አቅርቧል።

የሶማሌ ክልል የሰላምና አንድነት መድረክ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የሀገሪቱንና የክልሉን ወቅታዊ ጉዳዮች አስመለክቶ የጋራ አቋም አውጥቷል።

የመድረኩ አባላት የሆኑት የሶማሌ ክልል የሀገር ሽማግሌዎች ዛሬ በጅግጅጋ ከተማ ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ ባወጡት የጋራ መግለጫ እንደገለፁት፤ በሀገሪቱና ክልሉ ባለፉት 30 አመታት የነበሩ ዘርፈ ብዙ ችግሮችና መከራዎች ብዙ ዋጋን አስከፍለዋል ነው ያሉት።

ከለውጡ በኋላ በተለይ ባለፉት ሶስት አመታት የታየው ሰላምና ለውጥ በማስጠበቅ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል።

ባለፉት 30 አመታት በሶማሌ ክልል የነበረው እጅግ የከፋ ጭቆናና አፈና ከለውጡ በኋላ በመወገዱ ዜጎች አስተማማኝ ሰላም በማግኘታቸው ክልሉ ሰላምና ፀጥታ የሰፈነበት በመሆን፣ ለሀገሪቱም ተምሳሌት መሆን በመቻሉ ይህንን ለማወክ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች በጋራ መታገል እንደሚያስፈልግ ማሳሰባቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በሶማሌ ክልል ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘው አስተማማኝ ሰላምና ፀጥታ የበለጠ ለማስጠበቅ መንግሥት ሀላፊነት እንዳለበት በመገንዘብ ፀጥታውን ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱት ሀይሎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ አለበት ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.