Fana: At a Speed of Life!

የዳያስፖራው ማህበረሰብ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለህዳሴው ግድብ ግንባታ ከ700 ሺህ ዶላር በላይ ድጋፍ አድርጓል

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 8፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የዳያስፖራው ማህበረሰብ በ2012 በጀት ዓመት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 737 ሺህ 506 ዶላር ድጋፍ ማድረጉን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ።

የህዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን የዳያስፖራው ማህበረሰብ ከ42 ሚሊየን ዶላር በላይ ድጋፍ ማድረጉም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ለህዳሴ ግድብ ግንባታ የዳያስፖራው ድጋፍና ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል።

ከግድቡ ግንባታ ጋር በተያያዘ በተወሰኑ ጊዜያት መቀዛቀዝ እንደነበር አስታውሰው ከለውጡ በኋላ ግን ድጋፉ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።

የግድቡ ግንባታ ሂደት የነበሩበት ችግሮች ተወግደው በተሻለ ሁኔታ እየተከናወነ በመሆኑ እና የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌቱም መካሄዱ ትልቅ መነቃቃት መፍጠሩንም ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል።
በዲፕሎማሲው መስክ የተገኘው ስኬት ይበልጥ ተነሳሽነት እንዲኖር እንዳደረገ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.