Fana: At a Speed of Life!

የፌደራልና የክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮች ጉባዔ በሰመራ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 10ኛው የፌደራልና የክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮች ጉባዔ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በጉባዔው ላይ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ እና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀኔራል እንደሻው ጣሰውን ጨምሮ የሁሉም ክልሎች ፖሊስ ኮሚሽነሮች ተሳትፈዋል።

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ በጉባዔው ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፥ ሀገራዊ ምርጫው ግልፅና ተዓማኒ እንዲሆን የፖሊስ ሰራዊት በጠንካራ ዲሲፕሊን የተገነባ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

የፌደራል፣ የአዲስ አበባ ከተማ እና የድሬደዋ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽንን ጨምሮ የሁሉም ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነሮች በጉባዔው ላይ ሪፖርት እንደሚያቀርቡ ተገልጿል።

በዚህም በዋናነትም በየክልሉ ያሉ የህግ ማስከበር ደረጃ ምን ይመስላል፣ በህግ ማስከበር ሂደት ያጋጠሙ እግሮች እና በየክልሉ ያለው የፖሎስ ሰራዊት አደረጃጀትና ቁመና ምን መልክ አለው የሚለው ላይ እየተወያዩ ነው።

በተጨማሪም በ6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ የፀጥታ አካሉ ሰላምና ፀጥታን በማረጋገጥ ረገድ  የአዲስ አበባ እና የድሬደዋ ከተማን ጨምሮ የሁሉም ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምን ይመስላል የሚለውም ውይይት ይደረግበታል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሕን ለምርጫው እያደረገው ያለው ዝግጅትስ ምን ይመስላል የሚለው ላይም ምክክር እንደሚደረግ ነው የተገለፀው።

በፀጋዬ ንጉስ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.