Fana: At a Speed of Life!

በቻን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን ጋር ትጫወታለች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2022 ቻን የአፍሪካ አገራት ዋንጫ ውድድር የማጣሪያ ድልድል በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል።
 
በማጣሪያ ውድድሩ ላይ የምስራቅ እና መካከለኛ አፍሪካ (ሴካፋ) ሶስት ሀገራትን ወደ ዋናው ውድድር የሚያሳትፍ ሲሆን ÷በወጣው ድልድል መሰረት ኢትዮጵያ በመጀመሪያ ዙር ከደቡብ ሱዳን የምትጫወት ይሆናል፡፡
 
ይህንን የማጣሪያ ዙር ካለፈች ደግሞ ከሩዋንዳ ጋር በሁለተኛው ዙር ትጫወታለች፡፡
 
የመጀመሪያ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ ከሃምሌ 15 እስከ 17 ቀን 2014 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን÷ ሁለተኛው ጨዋታ ከሐምሌ 22 እስከ 24 ቀን 2014 ባሉት ቀናት እንደሚካሄድ የወጣው መርሐ ግብር ያመላክታል፡፡
 
ሁለተኛው ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ ደግሞ ከነሃሴ 20 እስከ 22 ቀን ፤መልስ ጨዋታው ደግሞ ከነሃሴ 27 እስከ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚካሄድ ካፍ አስታውቋል፡፡
 
የአገር ውስጥ ሊግ የሚጫወቱ ተጨዋቾችን ብቻ የሚያሳትፈው ውድድሩ በፈረንጆች 2023 ላይ በአልጄሪያ አስተናጋጅነት የሚካሄድ ሲሆን÷ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ በ2014 እና 2016 ውድድሮች ላይ ተሳታፊ እንደነበረች ከኢትጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.