Fana: At a Speed of Life!

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ለፍጻሜ ለማለፍ ዛሬ ተጠባቂ ጨዋታ ይደረጋል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ለፍፃሜ ለማለፍ በሚካሄደው የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ የፈረንሳዩ ፓሪስ ሴን ዠርሜ (ፒ ኤ ሲ ጂ) እና የጀርመኑ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡

ጨዋታው ምሽት 4 ሠዓት ላይ በፒ ኤስ ጂ ሜዳ ፓርክ ዴስ ፕሪንስ የሚከናወን ይሆናል፡፡

ባለፈው ሳምንት የተካሄደውን የመጀመሪያ ጨዋታ ዶርትሙንድ በሜዳው 1 ለ 0 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

በነገው ዕለት ደግሞ በመጀመሪያው ዙር የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ አሊያንዝ አሬና ላይ 2 አቻ የተለያዩት ሪያል ማድሪድና ባየርንሙኒክ የመልስ ጨዋታቸውን በማድሪድ ሳንትያጎ ቤርናቢዩ ላይ ያደርጋሉ፡፡

ዛሬ እና ነገ የሚካሄዱትን የደርሶ መልስ ጨዋታዎች ያሸነፉ ቡድኖች ለፍጻሜ እንደሚፋለሙም ከመርሐ-ግብሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የዘንድሮው የፍፃሜ ጨዋታ በፈረንጆቹ ሰኔ 1 ቀን 2024 በእንግሊዝ ዌምብሌይ ስታዲየም ይካሔዳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.