Fana: At a Speed of Life!

በሻምፒየንስ ሊጉ ከሪያል ማድሪድና ባየርሙኒክ ለፍጻሜ አላፊው ዛሬ ይለያል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ለፍፃሜ ለማለፍ በሚካሄደው የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ሪያል ማድሪድ እና ባየርንሙኒክ የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡

ጨዋታው ምሽት 4 ሠዓት ላይ በሪያል ማድሪድ ሜዳ ሳንትያጎ ቤርናቢዩ የሚከናወን ይሆናል፡፡

በመጀመሪያው ዙር የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ በባየርሙኒክ ሜዳ አሊያንዝ አሬና ስታዲየም 2 አቻ መለያየታቸው ይታወሳል፡፡

የዛሬው ጨዋታ አሸናፊ ትናንት ምሽት የፈረንሳዩን ፓሪስ ሴን ዠርሜ (ፒ ኤ ሲ ጂ) ከረታው የጀርመኑ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ጋር በፈረንጆቹ ሰኔ 1 ቀን 2024 በእንግሊዝ ዌምብሌይ ስታዲየም ለፍጻሜ የሚፋለሙ ይሆናል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.