Fana: At a Speed of Life!

ቅዱስ ጊዮርጊስ የዋናው ቡድን ዋና አሠልጣኝ አገደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ የዋናው ቡድን ዋና አሠልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታን ከማሰልጠን ተግባራቸው በጊዜዊነት አግዷል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ ዛሬ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የዋናውን ቡድን እንቅስቃሴ ገምግሟል፡፡

በዚህም አሠልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ የዋናው ቡድን ዋና አሠልጣኝ እና አሠልጣኝ ውብሸት ደሳለኝ የበረኞች አሠልጣኝ ተለዋጭ መመሪያ እስኪሰጥ ድረስ ከማሰልጠን ተግባራቸው ታግደው እንዲቆዩ ወስኗል።

በምትካቸውም አሠልጣኝ ደረጀ ተስፋዬ የዋናው ቡድን ም/አሠልጣኝ ዋና አሠልጣኝ ሆነው ከሚያዝያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በጊዜያዊነት እንዲያሠለጥኑ ተወስኗል፡፡

አሠልጣኝ ሳምሶን ሙሉጌታ ደግሞ የወጣት ቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ም/ አሠልጣኝ ሆነው በጊዜያዊነት እንዲያሠለጥኑ መወሰኑን የክለቡ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.