Fana: At a Speed of Life!

ጋምቢያ በእግር ኳስ ታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ ሩብ ፍጻሜን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፣ጥር 17፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በአፍሪካ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ውድድር ጋምቢያ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሩብ ፍፃሜውን መቀላቀል ችላለች፡፡
ትናንት ምሽት አንድ ሰዓት ላይ ጋምቢያ ከጊኒ ጋር ባደረገችዉ ጨዋታ በሙሳ ባሮ ብቸኛ ጎል 1 ለ 0 በማሸነፍ ነው በእግር ኳስ ታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን ሩብ ፍፃሜ መቀላቀል የቻለችዉ፡፡
በሌላ ጨዋታ የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ ሀገሯ ካሜሩን በኮቪድ-19 ወረርሽኝ በርካታ ተጫዋቾቿን ያጣችውን ኮሞሮስ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍፃሜው አልፋለች።
ካርል ቶኮ ኢካምቢ እና ቪሰንት አቡበከር የካሜሩንን የማሸነፊያ ጎሎች ከመረብ አሳርፈዋል።
ናጂም አብዱ በሰባተኛው ደቂቃ ላይ በኮሞሮስ በኩል ቀይ ካርድ ሲመለከት፥ በዘንድሮው አፍሪካ ዋንጫ ፈጣኑን ቀይ ካርድ የተመለከተው ተጫዋች ሆኗል።
የሁለቱን ሀገራት ጨዋታ ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል የመሐል ዳኛ ባምላክ ተሰማ በዋና ዳኝነት መርቶታል።
በቀጣይ የጋምቢያ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታውን ጥር 20 ቅዳሜ ከአዘጋጇ ካሜሮን ጋር ያደርጋል።
ጨዋታዎቹ ዛሬም ሲቀጥሉ በ2019ኙ የአፍሪካ ዋንጫ ሁለተኛ ሆና ያጠናቀቀችው ሴኔጋል ምሽት አንድ ሰዓት ላይ ኬፕ ቨርዴን ትገጥማለች፡፡
ከሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ ምሽት አራት ሰዓት ላይ ሞሮኮ ከማላዊ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ እንደሚሆንካፍ ኦንላይን ስፖርት ዘግቧል፡፡

በሚኪያስ አየለ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.