Fana: At a Speed of Life!

      ጎግል አዋኪ ያላቸውን 600 መተግበሪያዎች አገደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጎግል አዋኪ ያላቸውን 600 መተግበሪያዎች ማገዱን አስታወቀ።

ጎግል ከፕሌይ ስቶር ከተወገዱት 600 የአንድሮይድ መተግበሪያዎች ጋር ተያይዞ ተጠቃሚዎች ማስታወቂዎችን ክሊክ እንዲያደርጉ ክትትል የሚያደርጉ የመተግበሪያ አበልፃጊዎችንም አግዷል።

የኩባንያው የማስታወቂያ ቡድን ዋነኛ ትኩረት ከመተግበሪያ ውጭ የሚታዩ አዋኪ የሚባሉ ማስታወቂዎችን መለየት የሚያስችል አሰራርን መፍጠር ነው።

በማሳያነትም ከመተግበሪያው ይዘት ውጭ የሆነ ማስታወቂያ በአሁኑ ወቅት ጥቅም ላይ እየዋለ እንደማይገኝ ተጠቁሟል።

ኩባንያው ይህ አይነት አካሄድ የጎግልን ደንብና ፖሊሲ የጣሰ በመሆኑ 600ዎቹ መተግበሪያዎች እንደተወገዱ ነው ያስታወቀው።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ምርመራው እንደቀጠለ ያስታወቀው ኩባንያው በቀጣይም ህጉን የሚጥስ ካለ እርምጃው ይቀጥላል ብሏል።

ጎግል በፈረንጆቹ 2019 ህግና ደንብ ጥሰዋል ያላቸውን 10 ሺህ መተግበሪያዎችን እና አበልፃጊዎችን ማስወገዱን መረጃዎች ያመላክታሉ።

 

 

ምንጭ፦thehindu.com

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.