Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በስልክ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በስልክ ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን መግታት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስን ለመቀልበስ የሚያስችሉ ስራዎችን በማስተባበር በኩል እያከናወኑት ላለው ተግባር ምስጋና አቅርበዋል።

በቅርቡ ተግባራዊ በሚሆነው የፈረንሳይ-አፍሪካ እንቅስቃሴ ወደ ተጠናከረ ትብብር እንደሚያደርስ እምነታቸው መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ መሰል ትብብሮች እጅግ አስፈላጊ መሆናቸውን ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.