Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ በመጠንቀቅና ባለመዘናጋት ኮሮናን ማሸነፍ እንደሚገባ አስታወቁ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 21 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመጠንቀቅና ባለመዘናጋት የኮሮናቫይረን ማሸነፍ እንደሚገባ አስታወቁ።
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ቫይረሱን ይበልጥ በመጠንቀቅ እንዲሀጉም ባለመዘናጋት ማሸነፍና ማጥፋት እንደሚቻል አስታውቀዋል።
 
በመልዕክታቸውም “ኮሮና ከሚያሸንፈን እናሸንፈው፤ ከሚዘምትብን እንዝመትበት፤ ከሚያጠፋን እናጥፋው፤” ብለዋል።
 
መዘናጋት የኮሮናቫይረስ ወዳጅ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ “ኮሮና ከመዘናጋት ጋር ከተባበረ አንችለውም፤ ሁለቱን መነጣጠል አለብንም” ነው ያሉት።
 
መዘናጋት በመፈጠሩ ሳቢያም ሰሞኑን በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ ጥንቃቄ ለኮሮናቫይረስ እንደማይመችም ጠቅሰዋል።
 
ቫይረሱ “ጥንቃቄ ባለበት ወይ አይደርስም፤ ወይ የከፋ ጉዳት አያደርስምም” ነው ያሉት በመልዕክታቸው።
 
አሁን ላይ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከእኛ መዘናጋት ጋር በተያያዘ እየጨመረ መሆኑን አንስተው፥ ተባብሮ መነሳት እንደሚገባ ጠቁመዋል።
 
“ሁኔታው ሳይመርብን፣ እኛ እናምርበት። ኮሮና ሳያሸንፈን እናሸንፈው። ኮሮናን የማሸነፊያ ቀን ዛሬ፣ የማሸነፊያ ሰዓት አሁን፣ የሚያሸንፈውም ሰው እርስዎ ነዎት” ብለዋል።
 
ትናንት የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስቴር ባወጣው እለታዊ ሪፖርቱ በአንድ ቀን ብቻ 100 ሰዎች በሀገሪቱ የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።
 
ይህንንም ተከትሎ በሀገረቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 831 ደርሷል።
 
#FBC
 
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.