Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በአማራ ክልል 5 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የሚደረግባቸው የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአማራ ክልል 5 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ወጪ የሚደረግባቸው የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ አስጀመሩ፡፡

የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታው ከዱር ቤቴ ቁንዝላ-ሻሁራ-ፍንጅት ምዕራፍ አንድና ከገላጎ -ገንዳ ውሀ ምዕራፍ ሶስት ነው የሚካሄደው፡፡

የመንገድ ርዝመቱ 260 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር መሆኑም ተገልጿል፡፡

ከዱር -ቤቴ -ቁንዝላ ሻውራ -ፍንጅት ያለው የአስፓልት መንገድ ግንባታ 135 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን ከገላጎ ገንዳ ውሀ የአስፓልት መንገድ ግንባታ ደግሞ 125 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ነው።

የመንገዶቹ ግንባታ ወጭ በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ነው ተብሏል፡፡

የመንገዶቹ ግንባታ በቻይናው ዚ-ዥ-ያንግ ኮሙዩኒኬሽን ኮንስትራክሽን ግሩፕ ይከናወናል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.