Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመራጩ የኮንጎ ብራዛቪል ፕሬዚዳንት ዴኒስ ሳሱ ንጉኤሶ በዓለ ሲመት ላይ ተገኙ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመራጩ የኮንጎ ብራዛቪል ፕሬዚዳንት ዴኒስ ሳሱ ንጉኤሶ በዓለ ሲመት ላይ ተገኝተዋል።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በበዓለ ሲመቱ ላይ ለመታደም ከመጡ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ጋርም ተወያይተዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የኢትዮጵያ እውነት፣ የኢትዮ ሱዳን የድንበር ጉዳይ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ እና ምርጫ 2013ን በተመለከተ መረጃዎችን መለዋወጥ መቻላቸው ተገልጿል።

ፕሬዚዳንት ዴኒስ ሳሱ በበዓለ ሲመታቸው ላይ የተገኙ መሪዎችን አመስግነው የአህጉሪቱን የእርስ በእርስ ግንኙነት በማጠናከር በኩል እንደዚህ ያሉ መሰባሰቦች ፋይዳቸው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

በፕሬዚዳንቱ በዓለ ሲመት ላይ ከ20 በላይ ሀገራት በመሪዎች እና በተወካዮቻቸው መታደማቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዴኒስ ሳሱ ንጉኤሶ ከወራት በፊት በተካሄደው ምርጫ ማሸነፋቸው ይታወሳል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.