Fana: At a Speed of Life!

በ150 ሚሊዬን ዶላር ዘመናዊ ላቦራቶሪዎች በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ሊገነቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክልሎች እና በኢንስቲትዩቱ በ150 ሚሊየን ዶላር ዘመናዊ የሆኑ ላቦራቶሪዎች ግንባታ እና የአቅም ማጎልበት ስራዎቸን እንደሚጀምር የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
 
የላብራቶሪ ግንባታው እና የአቅም ማጎልበት ስራው ከዓለም ባንክ በተገኘ 150 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ እና ብድር እንደሆነ ተገልጿል።
 
የሚገነቡት ላብራቶሪዎች ዘመናዊ እና ደረጃቸውን የጠበቁ በመሆናቸው ከኢትዮጵያ አልፎ ለምስራቅ አፍሪካ ሀገራትም ጭምር አገልግሎት የመስጠት አቅም ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡
 
የፕሮጀክቱ ትግበራ በአራት ዋና ዋና መርሀ ግብሮች የተከፋፈለ ሲሆን በአንደኛው መርሀ ግብር የሀገሪቷን አጠቃላይ የላቦራቶሪ አቅም የመገንባት ስራዎች እንደሚከናወኑ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ ጠቁሟል።
 
በመሆኑም ደረጃ ሶስት ባዮ ሴፍቲ ብሔራዊ ሪፈረንስ ላብራቶሪ (BSL3) በኢንስቲትዩቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገነባ ሲሆን ይህም ላቦራቶሪ ከዚህ ቀደም በሀገሪቱ የሌለና በአቅምም ሆነ በአይነቱ አዲስ እንደሚሆነም ተገልጸል፡፡
 
ከዚህም በተጨማሪ 15 የክልል ሪፈረንስ ላቦራቶሪዎች የመገንባት እና ላቦራቶሪዎቹንም በመሳሪያ የማሟላት ስራዎች ይከናወናሉ ተብሎ ይጠበቃል።
 
በሌላም በኩል አሁን በሀገሪቷ በስራ ላይ ያሉ 8 ላቦራቶሪዎችም የአቅም ግንባታ እና በመሳሪያ የማዘመን ስራዎች እንደሚከናወኑላቸው ተጠቁሟል።
 
የላቦራቶሪ ግንባታ ከ3 እስከ 4 ዓመታት የሚፈጅ ሲሆን በየክልሉ የሚገነቡት 15 ላቦራቶሪዎች ግንባታ በሁለት ዓመት ውስጥ እንደሚጠናቀቁ ይጠበቃል፡፡
 
እነዚህ ላቦራቶሪዎች ወደ ስራ ሲገቡ ደግሞ ከዚህ ቀደም ወደ ውጭ አገር የሚላኩ ከፍተኛ ደህንነትን የሚጠይቁ የምርመራ ስራዎችን ያስቀራሉ ተብሏል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.